የቀጥታ ክፍል · በአማርኛ የሚሰጥ

ፕሮፌሽናል ቪዲዮዎችን በ AI ኤዲት ማድረግ ተማሩ፣ ኤዲተር መሆን ሳያስፈልጋችሁ

ቅድመ ምዝገባ አድርጉ

ስትመዘገቡ የራሳችሁ የክፍያ ገጽ ይከፈታል · ቦታ ውስን ነው

ምን እንደሚቀር፣ ምን እንደሚቆረጥ እና ምን ጎልቶ እንደሚታይ እናንተ ትወስናላችሁ። አድካሚውን ስራ — መቁረጡን፣ caption፣ ድምፁን እና motion graphics — AI ይሰራዋል። ለሁለት ቀን በቀጥታ online፣ በአማርኛ፣ እየሰራችሁ የምትማሩበት ክፍል ነው።

ምን ትማራላችሁ

ፕሮፌሽናል ኤዲቲንግ፣ በ AI

ከአጫጭር የ TikTok፣ Reels እና Shorts ቪዲዮዎች እስከ YouTube ቪዲዮዎችና ለሰዓታት የሚረዝሙ talking-head እና የኮርስ ቪዲዮዎች።

01

Rough cut እና caption

ጥሬ ቀረጻውን ወደ ንጹህ cut ትቀይራላችሁ። AI የተደጋገሙ ቦታዎችንና ዝምታዎችን ያገኛል፣ ከንግግሩ ጋር የሚሄድ caption ይጽፋል፤ መልኩን ደግሞ እናንተ ትመርጣላችሁ።

02

ከለር እና ድምፅ

የምትፈልጉትን በመግለጽ ብቻ ከለሩን ታስተካክላላችሁ፣ ድምፁን ታጠራላችሁ፣ ሙዚቃ ትጨምራላችሁ።

03

Motion graphics እና template

ርዕሶች፣ zoom፣ lower third እና የሚንቀሳቀስ ጽሑፍ፦ አንዴ እንደ template ሰርታችሁ በእያንዳንዱ ቪዲዮ ላይ ደግማችሁ ትጠቀሙበታላችሁ።

04

የራሳችሁ የኤዲቲንግ አሰራር

ደግማችሁ የምትጠቀሙበት አሰራር ይዛችሁ ትወጣላችሁ። AI አንዴ የእናንተን ስታይል ከተማረ በሚቀጥለው ቪዲዮ ላይ ራሱ ይደግመዋል።

ለማን ነው

ይህ ክፍል ለማን ነው?

  • የሶሻል ሚዲያ እና የዲጂታል ማርኬቲንግ ኤጀንሲዎች
  • በፍጥነት መስራት የሚፈልጉ ቪዲዮ ኤዲተሮች
  • ሶሻል ሚዲያ ማኔጀሮች እና ዲጂታል ማርኬተሮች
  • የራሳቸውን ቪዲዮ ኤዲት የሚያደርጉ content creators

ለሶሻል ሚዲያ ክሊፖች፣ ለYouTube ቪዲዮዎች፣ ለtalking-head ቪዲዮዎች፣ ለኮርስ ትምህርቶች፣ ለማስታወቂያዎችና ለደንበኛ ስራዎች ትጠቀሙበታላችሁ — አጭርም ይሁን ለሰዓታት የሚረዝም።

እንዴት ይሰራል

ክፍሉ እንዴት ይካሄዳል

01

ሁለት ቀን፣ በቀጥታ online

ክፍሉ ለሁለት ቀን በቀጥታ online፣ በአማርኛ ይሰጣል። በራሳችሁ ላፕቶፕ አብራችሁ እየሰራችሁ ትከታተላላችሁ፤ ጥያቄ ሲኖራችሁ እዚያው ትጠይቃላችሁ።

02

በትንንሽ ቡድኖች

እየሰሩ መማር ትንሽ ቡድን ይፈልጋል፤ ስለዚህ ሁሉም ሰው አሰራሩን ሲያዘጋጅ እርዳታ ያገኛል።

03

መጀመሪያ የሚሰሙት የተመዘገቡት ናቸው

ስትመዘገቡ የአሁኑ ዋጋና የክፍሉ ቀን ያለበት የራሳችሁ የክፍያ ገጽ ይደርሳችኋል። ከፍላችሁ proofኡን እዛው ታያይዛላችሁ፤ ከዛ የprivate groupኡ link ይደርሳችኋል።

ቅድመ ምዝገባ አድርጉ

አንድ ደቂቃ ብቻ ይወስዳል። ይህን መረጃ የምንጠቀመው ስለ ክፍሉ ልንነግራችሁ ብቻ ነው።

ክፍሉን ከተቀላቀላችሁ የቀጥታ ክፍሉን ሊንክ የምንልከው እዚህ ነው።

በመመዝገብ የግላዊነት ፖሊሲያችንን ትቀበላላችሁ።

ጥያቄዎች